• 1. በፀሐይና በብርሃኗ እምላለሁ፡፡

  • 2. በጨረቃም በተከተላት ጊዜ፤

  • 3. በቀኑም (ፀሐይን) በገለጻት ጊዜ፤

  • 4. በሌሊቱም በሸፈናት ጊዜ፤

  • 5. በሰማይቱም በገነባትም (ጌታ)፤

  • 6. በምድሪቱም በዘረጋትም፤

  • 7. በነፍስም ባስተካከላትም፤

  • 8. አመጽዋንና ፍርሃትዋንም ባሳወቃት (አምላክ እምላለሁ)፡፡

  • 9. (ከኀጢኣት) ያጠራት ሰው ፍላጎቱን በእርግጥ አገኘ፡፡

  • 10. (በኀጢኣት) የሸፈናትም ሰው በእውነት አፈረ፡፡

  • 11. ሠሙድ ወሰን በማለፍዋ አስተባበለች፡፡

  • 12. ጠማማዋ በተንቀሳቀሰ ጊዜ፡፡

  • 13. ለእነርሱም የአላህ መልክተኛ (ሷሊህ) «የአላህን ግመል የመጠጥ ተራዋንም (ተጠንቀቁ)» አላቸው፡፡

  • 14. አስተባበሉትም፡፡ (ቋንጃዋን) ወጓትም፡፡ በኀጢኣታቸውም ምክንያት ጌታቸው (ቅጣትን) በእነርሱ ላይ ደመደመባቸው፤ አስተካከላትም፡፡

  • 15. ፍጻሜዋንም (የምታስከትለውን) አያፈራም፡፡

ሼር ያድርጉ
logo
logo
logo
logo