• 1. ለሃሜተኛ ለዘላፊ ሁሉ ወዮለት፡፡

  • 2. ለዚያ ገንዘብን የሰበሰበና የቆጣጠረው (ያደለበውም) ለኾነ ፤(ወዮለት)፡፡

  • 3. ገንዘቡ የሚያዘወትረው መኾኑን ያስባል፡፡

  • 4. ይከልከል፤ በሰባሪይቱ (እሳት) ውስጥ በእርግጥ ይጣላል፡፡

  • 5. ሰባሪይቱም ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ?

  • 6. የተነደደችው የአላህ እሳት ናት፡፡

  • 7. ያቺ በልቦች ላይ የምትዘልቅ የኾነችው፡፡

  • 8. እርሷ በእርግጥ በእነርሱ ላይ የተዘጋጀች ናት፡፡

  • 9. በተዘረጋች አዕማድ ውስጥ (የተዘጋች ናት)፡፡

ሼር ያድርጉ
logo
logo
logo
logo