• 1. በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡

  • 2. ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው፤

  • 3. እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ

  • 4. የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው፡፡

  • 5. አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡

  • 6. ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፡፡

  • 7. የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን፤ በሉ)፡፡

ሼር ያድርጉ
logo
logo
logo
logo