HARUN YAHYA
Amharic / አማርኛ
AM
ቁርኣን
سورة الملك
1. ያ ንግሥና በእጁ የኾነው አምላክ ችሮታው በዛ፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡
2. ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መኾኑን ሊሞክራችሁ ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ ነው፡፡ እርሱም አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡
3. ያ ሰባትን ሰማያት የተነባበሩ ኾነው የፈጠረ ነው፡፡ በአልረሕማን አፈጣጠር ውስጥ ምንም መዛነፍን አታይም፡፡ ዓይንህንም መልስ፡፡ «ከስንጥቆች አንዳችን ታያለህን?»
4. ከዚያም ብዙ ጊዜ ዓይንህን መላልስ፡፡ ዓይንህ ተዋርዶ እርሱም የደከመ ኾኖ ወዳንተ ይመለሳል፡፡
5. ቅርቢቱን ሰማይም በእርግጥ በመብራቶች (በከዋክብት) አጌጥናት፡፡ ለሰይጣናትም መቀጥቀጫዎች አደረግናት፡፡ ለእነርሱም (ለሰይጣኖች) የእሳትን ቅጣት አዘጋጀን፡፡
6. ለእነዚያም በጌታቸው ለካዱት የገሀነም ቅጣት አልላቸው፡፡ መመለሻይቱም ከፋች!
7. በውስጧ በተጣሉ ጊዜ፤ እርሷ የምትፈላ ስትኾን ለእርሷ (እንደ አህያ) ማናፋትን ይሰማሉ፡፡
8. ከቁጭትዋ የተነሳ ልትቆራረጥ ትቀርባለች፡፡ በውስጧ ጭፍሮች በተጣሉ ቁጥር ዘበኞችዋ «አስፈራሪ (ነቢይ) አልመጣችሁምን?» በማለት ይጠይቋቸዋል፡፡
9. «አይደለም በእርግጥ አስፈራሪ መጥቶናል፡፡ አስተባበልንም፡፡ አላህም ምንንም አላወረደ እናንተ (አውርዷል ስትሉ) በትልቅ ስህተት ውስጥ እንጅ አይደላችሁም አልን» ይላሉ፡፡
10. «የምንሰማ ወይም የምናስብ በነበርንም ኖሮ በነዳጅ እሳት ጓዶች ውስጥ ባልኾን ነበር» ይላሉ፡፡
11. በኀጢኣታቸውም ያምናሉ ለእሳት ጓዶችም (ከእዝነት) መራቅ ተገባቸው፡፡
12. እነዚያ ጌታቸውን በሩቁ የሚፈሩ ለእነርሱ ምሕረትና ታላቅ ምንዳ አልላቸው፡፡
13. (ሰዎች ሆይ!) ቃላችሁንም መስጥሩ፡፡ ወይም በእርሱ ጩሁ፡፡ እርሱ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
14. የፈጠረ አምላክ እርሱ ዕውቀት ረቂቁ፣ ውስጥ ዐዋቂው ሲኾን (ምስጢርን ሁሉ) አያውቅምን?
15. እርሱ ያ ምድርን ለእናንተ የተገራች ያደረገላችሁ ነው፡፡ በጋራዎችዋና በመንገዶችዋም ኺዱ፡፡፡ ከሲሳዩም ብሉ፡፡ (ኋላ) መመለሻውም ወደእርሱ ብቻ ነው፡፡
16. በሰማይ ውስጥ ያለን (ሰራዊት) በእናንተ ምድርን ቢደረባባችሁ ወዲያውም እርሷ የምታረገርግ ብትኾን ትተማመናላችሁን? (አትፈሩምን?)
17. ወይም በሰማይ ውስጥ ያለን በእናንተ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን ቢልክባችሁ ትተማመናላችሁን? (አትፈሩምን?) ማስጠንቀቄም እንዴት እንደኾነ ወደፊት ታውቃላችሁ፡፡
18. እነዚያም ከእነርሱ በፊት የነበሩት በእርግጥ አስተባበሉ፡፡ ጥላቻዬም እንዴት ነበር!
19. ወደ አእዋፍ ከበላያቸው ክንፎቻቸውን ዘርግተው ተንሳፋፊዎች የሚሰበሰቡም ሲኾኑ አላዩምን? ከአልረሕማን በቀር (ባየር ላይ) የሚይዛቸው የለም፡፡ እርሱ በነገሩ ሁሉ ተመልካች ነው፡፡
20. በእውነቱ ያ እርሱ ከአልረሕማን ሌላ የሚረዳችሁ ለእናንተ የኾነ ሰራዊት ማነው? ከሓዲዎች በመታለል ውስጥ እንጅ በሌላ ላይ አይደሉም፡፡
21. ወይም ሲሳዩን ቢይዝባችሁ ያ ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማነው? በእውነቱ እነርሱ በሞገድና በመደንበር ውስጥ ችክ አሉ፡፡
22. በፊቱ ላይ ተደፍቶ የሚኼድ ሰው ይበልጥ የቀና ነውን? ወይስ በቀጥተኛ መንገድ ላይ ተስተካክሎ የሚኼድ?
23. «እርሱ ያ የፈጠራችሁ ለእናንተም መስሚያና ማያዎችን፣ ልቦችንም ያደረገላችሁ ነው፡፡ ጥቂትንም አታመስግኑም» በላቸው፡፡
24. «እርሱ ያ በምድር ላይ የበተናቸሁ ነው፡፡ ወደእርሱም ትሰበሰባላችሁ» በላቸው፡፡
25. «እውነተኞችም እንደኾናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው?» ይላሉ፡፡
26. «ዕውቀቱ አላህ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ እኔ ግልጽ አስፈራሪ እንጅ ሌላ አይደለሁም» በላቸው፡፡
27. (ቅጣቱን) ቅርብ ኾኖ ባዩትም ጊዜ የእነዚያ የካዱት ሰዎች ፊቶች ይክከፋሉ፡፡ «ይህ ያ በእርሱ ትከራከሩበት የነበራችሁት ነው» ይባላሉም፡፡
28. «አያችሁን? አላህ ቢገድለኝ ከእኔ ጋር ያሉትንም (እንደዚሁ) ወይም (በማቆየት) ቢያዝንልን ከሓዲዎችን ከአሳማሚ ቅጣት የሚያድን ማን ነው?» በላቸው፡፡
29. «እርሱ (እመኑበት የምላችሁ) አልረሕማን ነው፡፡ (እኛ) በእርሱ አመንን፡፡ በርሱም ላይ ተጠጋን፡፡ ወደ ፊትም በግልጽ መሳሳት ውስጥ የኾነው እርሱ ማን አንደ ኾነ በእርግጥ ታውቃላችሁ» በላቸው፡፡
30. «አያችሁን? ውሃችሁ ሠራጊ ቢኾን ፈሳሺን ውሃ የሚያመጣላቸሁ ማን ነው?» በላቸው፡፡ (አላህ የዓለማት ጌታ ያመጣዋል)፡፡
ሼር ያድርጉ
1. ورَةُ الْفَاتِحَة
2. ورَةُ البقرة
3. سُورَةُ آل عمران
4. سورة النساء
5. سورۃ المائدة
6. سورة الأنعام
7. سورة الاعراف
8. سورۃ الانفال
9. سورة التوبة
10. سورة يونس
11. سورۃ ھود
12. سورة يوسف
13. سورة الرعد
14. سورة ابراهيم
15. سورة الحجر
16. سورة النحل
17. سورة الإسراء
18. سورة الكهف
19. سورة مريم
20. سورة طه
21. سورة الأنبياء
22. سورة الحج
23. سورة المؤمنون
24. سورة النور
25. سورة الفرقان
26. سورة الشعراء
27. سورة النمل
28. سورة القصص
29. سورة العنكبوت
30. سورة الروم
31. سورة لقمان
32. سورة السجدة
33. سورة الأحزاب
34. سورة سبإ
35. سورة فاطر
36. سورةيس
37. سورة الصافات
38. سورة ص
39. سورة الزمر
40. سورة غافر
41. سورة فصلت
42. سورة الشورى
43. سورة الزخرف
44. سورة الدخان
45. سورة الجاثية
46. سورة الأحقاف
47. سورة محمد
48. سورة الفتح
49. ورة الحجرات
50. سورة ق
51. سورة الذاريات
52. سورة الطور
53. سورة النجم
54. سورة القمر
55. سورة الرحمن
56. سورة الواقعة
57. سورة الحديد
58. سورة المجادلة
59. سورة الحشر
60. سورة الممتحنة
61. سورة الصف
62. سورة الجمعة
63. سورة المنافقون
64. سورة التغابن
65. سورة الطلاق
66. سورة التحريم
67. سورة الملك
68. سورة القلم
69. سورة الحاقة
70. سورة المعارج
71. سورة نوح
72. سورة الجن
73. سورة المزمل
74. سورة المدثر
75. سورة القيامة
76. سورة الانسان
77. سورة المرسلات
78. سورة النبإ
79. سورة النازعات
80. سورة عبس
81. سورة التكوير
82. سورة الإنفطار
83. سورة المطففين
84. سورة الإنشقاق
85. سورة البروج
86. سورة الطارق
87. سورة الأعلى
88. سورة الغاشية
89. سورة الفجر
90. سورة البلد
91. سورة الشمس
92. سورة الليل
93. سورة الضحى
94. سورة الشرح
95. سورة التين
96. سورة العلق
97. سورة القدر
98. سورة البينة
99. سورة الزلزلة
100. سورة العاديات
101. سورة القارعة
102. Aسورة التكاثر
103. سورة العصر
104. سورة الهمزة
105. سورة الفيل
106. سورة قريش
107. سورة الماعون
108. سورة الكوثر
109. سورة الكافرون
110. سورة النصر
111. سورة المسد
112. سورة الإخلاص
113. سورة الفلق
114. سورة الناس