• 1. በሰማዩ በሌሊት መጪውም እምላለሁ፡፡

  • 2. የሌሊት መጪውም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?

  • 3. ጨለማን ቀዳጁ ኮከብ ነው፡፡

  • 4. ነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡

  • 5. ሰውም ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት፡፡

  • 6. ከተስፈንጣሪ ውሃ ተፈጠረ፡፡

  • 7. ከጀርባና ከእርግብግብቶች መካከል የሚወጣ ከኾነ (ውሃ)፡፡

  • 8. እርሱ (አላህ) በመመለሱ ላይ በእርግጥ ቻይ ነው፡፡

  • 9. ምስጢሮች በሚገለጡበት ቀን፡፡

  • 10. ለእርሱም (ለሰው) ኀይልና ረዳት ምንም የለውም፡፡

  • 11. የመመለስ ባለቤት በኾነችው ሰማይም እምላለሁ፡፡

  • 12. (በበቃይ) የመሰንጠቅ ባለቤት በኾነችው ምድርም፤

  • 13. እርሱ (እውነትን ከውሸት) የሚለይ ቃል ነው፡፡

  • 14. እርሱም ቀልድ አይደለም፡፡

  • 15. እነርሱ በእርግጥ ተንኮልን ይሠራሉ፡፡

  • 16. (እኔ) ተንኮልንም እመልሳለሁ፡፡

  • 17. ከሓዲዎችንም ቀን ስጣቸው፡፡ ጥቂትን ጊዜ አቆያቸው፡፡

ሼር ያድርጉ
logo
logo
logo
logo