HARUN YAHYA
Amharic / አማርኛ
AM
ቁርኣን
سورة الدخان
1. ሐ.መ (ሓ ሚም)፡፡
2. አብራሪ በኾነው መጽሐፍ እንምላለን፡፡
3. እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው፡፡ እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና፡፡
4. በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል፡፡
5. ከእኛ ዘንድ የኾነ ትእዛዝ ሲኾን (አወረድነው)፡፡ እኛ (መልክተኞችን) ላኪዎች ነበርን፡፡
6. ከጌታህ በኾነው ችሮታ (ተላኩ)፡፡ እነሆ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡
7. የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ነገር ሁሉ ጌታ ከኾነው (ተላኩ)፡፡ የምታረጋግጡ እንደኾናችሁ (ነገሩ እንዳልነው መኾኑን እወቁ)፡፡
8. ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ያደርጋል፡፡ ይገድላልም፡፡ ጌታችሁ የመጀመሪያዎቹ አባቶቻችሁም ጌታ ነው፡፡
9. በእውነቱ እነርሱ የሚጫወቱ ሲኾኑ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡
10. ሰማይም በግልጽ ጭስ የምትመጣበትን ቀን ተጠባበቅ፡፡
11. ሰዎችን የሚሸፍን (በኾነ ጭስ) ይህ አሳማሚ ቅጣት ነው፡፡
12. «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ላይ ቅጣቱን ግለጥልን፡፡ እኛ አማኞች እንኾናለንና» (ይላሉም)፡፡
13. (ቅጣቱ በወረደ ጊዜ) ለእነርሱ መግገሰጽ እንዴት ይኖራቸዋል? አስረጅ መልክተኛ የመጣቸው ሲኾን (የካዱም ሲኾኑ)፡፡
14. ከዚያም ከእርሱ የዞሩ፤ (ከሰው) «የተሰተማረ ዕብድ ነው» ያሉም ሲኾኑ፡፡
15. እኛ ቅጣቱን ለጥቂት ጊዜ ገላጮች ነን፡፡ እናንተ (ወደ ክህደታችሁ) በእርግጥ ተመላሾች ናችሁ፡፡
16. ታላቂቱን ብርቱ አያያዝ በምንይዝበት ቀን፤ እኛ ተበቃዮች ነን፡፡
17. ከእነርሱም በፊት የፈርዖንን ሕዝቦች በእርግጥ ሞከርን፡፡ ክቡር መልእክተኛም መጣላቸው፡፡
18. «የአላህን ባሮች ወደኔ አድርሱ፡፡ እኔ ለእናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝና፡፡
19. «በአላህም ላይ አትኩሩ፡፡ እኔ ግልጽ የኾነን አስረጅ ያመጣሁላችሁ ነኝና (በማለት መጣላቸው)፡፡
20. «እኔም እንዳትወግሩኝ በጌታየና በጌታችሁ ተጠብቂያለሁ፡፡
21. «በእኔም ባታምኑ ራቁኝ» (ተዉኝ አለ)፡፡
22. ቀጥሎም (ስለ ዛቱበት) «እነዚህ አመጸኞች ሕዝቦች ናቸው» (አጥፋቸው) ሲል ጌታውን ለመነ፡፡
23. (ጌታው) «ባሮቼንም ይዘህ በሌሊት ኺድ፡፡ እናንተ የሚከተሉዋችሁ ናችሁና፡፡
24. «ባሕሩንም የተከፈተ ኾኖ ተወው፡፡ እነርሱ የሚሰጥጠሙ ሰራዊት ናቸውና» (አለው)፡፡
25. ከአትክልቶችና ከምንጮችም ብዙ ነገሮችን ተዉ፡፡
26. ከአዝመራዎችም ከመልካም መቀመጫም፡፡
27. በእርሷ ተደሳቾች ከነበሩባትም ድሎት (ብዙን ነገር ተዉ)፡፡
28. (ነገሩ) እንደዚሁ ኾነ፡፡ ሌሎችንም ሕዝቦች አወረስናት፡፡
29. ሰማይና ምድርም በእነርሱ ላይ አላለቀሱም፡፡ የሚቆዩም አልነበሩም፡፡
30. የእስራኤልንም ልጆች አዋራጅ ከኾነ ስቃይ በእርግጥ አዳንናቸው፡፡
31. ከፈርዖን፤ እርሱ የኮራ ከወሰን አላፊዎቹ ነበርና፡፡
32. ከማወቅም ጋር በዓለማት ላይ በእርግጥ መረጥናቸው፡፡
33. ከታምራቶችም በውስጡ ግልጽ የኾነ ፈተና ያለበትን ሰጠናቸው፡፡
34. እነዚህ (የመካ ከሓዲዎች) በእርግጥ ይላሉ፡-
35. እርሷ የፊተኛይቱ ሞታችን እንጅ አይደለችም፡፡ እኛም የምንቀሰቀስ አይደለንም፡፡
36. እውነተኞችም እንደ ኾናችሁ አባቶቻችንን አምጡልን፡፡
37. እነርሱ በላጮች ናቸውን ወይስ የቱብበዕ ሕዝቦችና እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት? አጠፋናቸው፡፡ እነርሱ አመጸኞች ነበሩና፡፡
38. ሰማያትንና ምድርንም በሁለቱ መካከል ያለውንም ሁሉ ቀላጆች ኾነን አልፈጠርንም፡፡
39. ሁለቱንም በምር እንጅ አልፈጠርናቸውም፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡
40. የመለያው ቀን ለሁሉም ቀጠሯቸው ነው፡፡
41. ዘመድ ከዘመዱ ምንንም የማይጠቅምበት እነርሱም የማይርረዱበት ቀን ነው፡፡
42. አላህ ያዘነለት ሰውና ያመነ ብቻ ሲቀር፡፡ (እርሱስ ይርረዳል)፡፡ እርሱ አሸናፊው አዛኙ ነውና፡፡
43. የዘቁመ ዛፍ
44. የኀጢኣተኛው ምግብ ነው፡፡
45. እንደ ዘይት አተላ ነው፡፡ በሆዶች ውስጥ የሚፈላ ሲኾን፡፡
46. እንደ ገነፈለ ውሃ አፈላል (የሚፈላ ሲኾን)፡፡
47. ያዙት፤ ወደ ገሀነም መካከልም በኀይል ጎትቱት፡፡
48. ከዚያም «ከራሱ በላይ ከፈላ ውሃ ስቃይ አንቧቡበት፡፡»
49. «ቅመስ፤ አንተ አሸናፊው ክብሩ ነህና» (ይባላል)፡፡
50. «ይህ ያ በእርሱ ትጠራጠሩበት የነበራችሁት ነው» (ይባላሉ)፡፡
51. ጥንቁቆቹ በእርግጥ በጸጥተኛ መኖሪያ ውስጥ ናቸው፡፡
52. በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡
53. ፊት ለፊት የተቅጣጩ ኾነው ከስስ ሐርና ከወፍራም ሐር ይለብሳሉ፡፡
54. (ነገሩ) እንደዚሁ ነው፤ ዓይናማዎች የኾኑን ነጫጭ ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን፡፡
55. በእርሷም ውስጥ የተማመኑ ኾነው፤ ከፍራፍሬ ሁሉ ያዝዛሉ፡፡
56. የፊተኛይቱን ሞት እንጅ (ዳግመኛ) በእርሷ ውስጥ ሞትን አይቀምሱም፡፡ የገሀነምንም ቅጣት (አላህ) ጠበቃቸው፡፡
57. ከጌታህ በኾነ ችሮታ (ጠበቃቸው)፡፡ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡
58. (ቁርኣኑን) በቋንቋህም ያገራነው (ሕዝቦችህ) ይገነዘቡ ዘንድ ብቻ ነው፡፡
59. ተጠባበቅም እነርሱ ተጠባባቂዎች ናቸውና፡፡
ሼር ያድርጉ
1. ورَةُ الْفَاتِحَة
2. ورَةُ البقرة
3. سُورَةُ آل عمران
4. سورة النساء
5. سورۃ المائدة
6. سورة الأنعام
7. سورة الاعراف
8. سورۃ الانفال
9. سورة التوبة
10. سورة يونس
11. سورۃ ھود
12. سورة يوسف
13. سورة الرعد
14. سورة ابراهيم
15. سورة الحجر
16. سورة النحل
17. سورة الإسراء
18. سورة الكهف
19. سورة مريم
20. سورة طه
21. سورة الأنبياء
22. سورة الحج
23. سورة المؤمنون
24. سورة النور
25. سورة الفرقان
26. سورة الشعراء
27. سورة النمل
28. سورة القصص
29. سورة العنكبوت
30. سورة الروم
31. سورة لقمان
32. سورة السجدة
33. سورة الأحزاب
34. سورة سبإ
35. سورة فاطر
36. سورةيس
37. سورة الصافات
38. سورة ص
39. سورة الزمر
40. سورة غافر
41. سورة فصلت
42. سورة الشورى
43. سورة الزخرف
44. سورة الدخان
45. سورة الجاثية
46. سورة الأحقاف
47. سورة محمد
48. سورة الفتح
49. ورة الحجرات
50. سورة ق
51. سورة الذاريات
52. سورة الطور
53. سورة النجم
54. سورة القمر
55. سورة الرحمن
56. سورة الواقعة
57. سورة الحديد
58. سورة المجادلة
59. سورة الحشر
60. سورة الممتحنة
61. سورة الصف
62. سورة الجمعة
63. سورة المنافقون
64. سورة التغابن
65. سورة الطلاق
66. سورة التحريم
67. سورة الملك
68. سورة القلم
69. سورة الحاقة
70. سورة المعارج
71. سورة نوح
72. سورة الجن
73. سورة المزمل
74. سورة المدثر
75. سورة القيامة
76. سورة الانسان
77. سورة المرسلات
78. سورة النبإ
79. سورة النازعات
80. سورة عبس
81. سورة التكوير
82. سورة الإنفطار
83. سورة المطففين
84. سورة الإنشقاق
85. سورة البروج
86. سورة الطارق
87. سورة الأعلى
88. سورة الغاشية
89. سورة الفجر
90. سورة البلد
91. سورة الشمس
92. سورة الليل
93. سورة الضحى
94. سورة الشرح
95. سورة التين
96. سورة العلق
97. سورة القدر
98. سورة البينة
99. سورة الزلزلة
100. سورة العاديات
101. سورة القارعة
102. Aسورة التكاثر
103. سورة العصر
104. سورة الهمزة
105. سورة الفيل
106. سورة قريش
107. سورة الماعون
108. سورة الكوثر
109. سورة الكافرون
110. سورة النصر
111. سورة المسد
112. سورة الإخلاص
113. سورة الفلق
114. سورة الناس