1. (ሙሐመድ ሆይ!) በል «እነሆ ከጂን የኾኑ ጭፈሮች (ቁርኣንን) አዳመጡ፡፡‹እኛ አስደናቂ የኾነን ቁርኣን ሰማንም› አሉ ማለት ወደእኔ ተወረደ፡፡
2. ‹ወደ ቀጥታ መንገድ የሚመራን (ቁርአን ሰማን)፡፡ በእርሱም አመንን፡፡ በጌታችንም አንድንም አናጋራም፡፡›
3. ‹እነሆም የጌታችን ክብር ላቀ፡፡ ሚስትንም ልጅንም አልያዘም፡፡›
4. ‹እነሆም ቂላችን በአላህ ላይ ወሰን ያለፈን (ውሸት) ይናገር ነበር፡፡›
5. ‹እኛም ሰዎችና ጋኔኖች በአላህ ላይ ውሸትን (ቃል) አይናገሩም ማለትን ጠረጠርን፡፡›
6. ‹እነሆም ከሰዎች የኾኑ ወንዶች በጋኔን ወንዶች ይጠበቁ ነበሩ፡፡ ኩራትንም ጨመሩዋቸው፡፡›
7. ‹እነርሱም አላህ አንድንም አይቀሰቅስም ማለትን እንደጠረጠራችሁ ጠረጠሩ፡፡›
8. ‹እኛም ሰማይን (ለመድረስ) ፈለግን፡፡ ብርቱ ጠባቂዎችንና ችቦዎችንም ተሞልታ አገኘናት፡፡
9. ‹እኛም ከእርሷ (ወሬን) ለማደመጥ በመቀመጫዎች እንቀመጥ ነበርን፡፡ አሁን ግን የሚያዳምጥ ሰው ለእርሱ ተጠባባቂ ችቦን ያገኛል፡፡
10. ‹እኛም በምድር ውስጥ ባልሉ ሰዎች ክፉ ተሽቷል? ወይስ በእነርሱ ጌታቸው ደግን ነገር ሽቷል? ማለትን አናውቅም፡፡
11. ‹እኛም ከእኛ ውስጥ ደጎች አልሉ፡፡ ከኛም ከዚህ ሌላ የኾኑ አልሉ፡፡ የተለያዩ መንገዶች (ባለ ቤቶች) ነበርን፡፡
12. ‹እኛም አላህን በምድር ውስጥ ፈጽሞ የማናቅተው፤ ሸሽተንም ፈጽሞ የማናመልጠው መኾናችንን አረጋገጥን፡፡
13. ‹እኛም መሪውን በሰማን ጊዜ በርሱ አመንን፡፡ በጌታውም የሚያምን ሰው መግጎደልንም መጭጨመርንም አይፈራም፡፡
14. «እኛም ከእኛ ውስጥ ሙስሊሞች አልሉ፡፡ ከእኛም ውስጥ በዳዮች አልሉ፡፡ የሰለሙም ሰዎች እነዚያ ቅንን መንገድ መረጡ፡፡»
15. በዳዮቹማ ለገሀነም ማገዶ ኾኑ፡፡
16. እነሆም በመንገዲቱ ላይ ቀጥ ባሉ ኖሮ ብዙ ዝናምን ባጠጣናቸው ነበር (ማለትም ተወረደልኝ)፡፡
17. በእርሱ ልንሞክራቸው (ባጠጣናቸው ነበር)፡፡ ከጌታውም ማስታወሻ የሚያፈገፍግ ሰው አስቸጋሪን ቅጣት ያገባዋል፡፡
18. እነሆ መስጊዶችም የአላህ ብቻ ናቸው፡፡ (በውስጣቸው) ከአላህ ጋር አንድንም አትገዙ (ማለትም)፡፡
19. እነሆም የአላህ ባሪያ (ሙሐመድ አላህን) የሚጠራው ኾኖ በተነሳ ጊዜ (ጋኔኖች) በእርሱ ላይ ድርብርቦች ሊኾኑ ቀረቡ (ማለትም)፡፡
20. «እኔ የምግገዛው ጌታየን ብቻ ነው፡፡ በእርሱም አንድንም አላጋራም» በል፡፡
21. «እኔ ለእናንተ ጉዳትንም ቀጥታንም አልችልም» በላቸው፡፡
22. «እኔ ከአላህ (ቅጣት) አንድም አያድነኝም፡፡ ከእርሱም ሌላ መጠጊያን አላገኝም» በላቸው፡፡
23. «ከአላህ የኾነ ማድረስን መልክቶቹንም በስተቀር (አልችልም)፡፡ አላህንና መልክተኛውንም የሚያምጽ ሰው ለእርሱ የገሀነም እሳት አልለው፡፡ በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ሲኾኑ፡፡»
24. የሚስፈራሩበትንም ባዩ ጊዜ ረዳቱ ደካማ፣ ቁጥሩም አነስተኛ የኾነው ማን እንደኾነ በእርግጥ ያውቃሉ፡፡
25. «የምትስፈራሩበት ነገር ቅርብ ወይም ጌታየ ለእርሱ የተወሰነ ጊዜን የሚያደርግለት (ሩቅ) መኾኑን አላውቅም» በላቸው፡፡
26. «(እርሱ) ሩቁን ምስጢር ዐዋቂ ነው፡፡ በምስጢሩም ላይ አንድንም አያሳውቅም፡፡»
27. ከመልክተኛ ለወደደው ቢኾን እንጅ (ለሌላ አይገልጽም)፡፡ እርሱም ከስተፊቱም ከስተኋላውም ጠባቂዎችን ያደርግለታል፡፡
28. እነርሱ ዘንድ ባለው ነገር ዕውቀቱ የከበበና ነገሩንም ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ሲኾን የጌታቸውን መልክቶች ያደረሱ መኾናቸውን ያውቅ ዘንድ (ጠባቂ ያደርጋል)፡፡