• 1. ነ.(ኑን)፤ በብርእ እምላለሁ በዚያም (መልአኮች) በሚጽፉት፡፡
  • 2. አንተ በጌታህ ጸጋ የተጎናጸፍክ ስትኾን ዕብድ አይደለህም፡፡
  • 3. ላንተም (ከጌታህ) የማይቋረጥ ዋጋ በእርግጥ አልለህ፡፡
  • 4. አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ፡፡
  • 5. ወደፊትም ታያለህ፤ ያያሉም፡፡
  • 6. ዕብደት በማንኛችሁ እንዳልለ፡፡
  • 7. ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ተመሪዎቹን ዐዋቂ ነው፡፡
  • 8. ለአስተባባዮችም አትታዝዙ፡፡
  • 9. ብትመሳሰላቸውና ቢመሳሰሉህ ተመኙ፡፡
  • 10. ወራዳንም ሁሉ አትታዘዝ፡፡
  • 11. ሰውን አነዋሪንና በማሳበቅ ኼያጅን፡፡
  • 12. ለበጎ ነገር በጣም ከልካይን፣ ወሰን አላፊን፣ ኃጢአተኛን፤
  • 13. ልበ ደረቅን፣ ከዚህ በኋላ ዲቃላን (ሁሉ አትታዘዝ)፡፡
  • 14. የገንዘብና የልጆች ባለቤት በመኾኑ (ያስተባብላል)፡፡
  • 15. በእርሱ ላይ አንቀጾቻችን በሚነበቡ ጊዜ «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው» ይላል፡፡
  • 16. በአፍንጫው ላይ በእርግጥ (የሚነወርበት) ምልክት እናደርግበታለን፡፡
  • 17. እኛ የአትክልቲቱን ባለቤቶቸ እንደ ሞከርን (የመካን ሰዎች) ሞከርናቸው፡፡ ማልደው (ፍሬዋን) ሊለቅሟት በማሉ ጊዜ፡፡
  • 18. (በመሓላቸው) አያስቀሩምም፡፡
  • 19. እነርሱ የተኙ ኾነውም ሳሉ ከጌታህ የኾነ ዟሪ በእርሷ ላይ ዞረባት፡፡
  • 20. እንደ ሌሊት ጨለማም ኾና አነጋች፤ (ከሰለች)፡፡
  • 21. ያነጉም ኾነው ተጠራሩ፡፡
  • 22. «ቆራጮች እንደ ኾናችሁ በእርሻቸሁ ላይ ማልዱ» በማለት፡፡
  • 23. እነርሱ የሚንሾካሾኩ ኾነው ኼዱም፡፡
  • 24. ዛሬ በእናንተ ላይ ድኻ እንዳይገባት በማለት፡፡
  • 25. (ድኾችን) በመከልከልም ላይ (በሐሳባቸው) ቻዮች ኾነው ማለዱ፡፡
  • 26. (ተቃጥላ) ባዩዋትም ጊዜ «እኛ በእርግጥ ተሳሳቾች ነን» አሉ፡፡
  • 27. «ይልቁንም እኛ የተከለከልን ነን» አሉ፡፡
  • 28. ትክክለኛቸው «ለእናንተ አላህን ለምን አታጠሩም አላልኳችሁምን?» አላቸው፡፡
  • 29. «ጌታችን ጥራት ይገባው፡፡ እኛ በዳዮች ነበርን፤» አሉ፡፡
  • 30. የሚወቃቀሱም ኾነው ከፊሎቻቸው በከፊሉ ላይ መጡ፡፡
  • 31. «ዋ ጥፋታችን! እኛ ድንበር አላፊዎች ነበርን፤» አሉ፡፡
  • 32. «ጌታችን ከእርሷ የተሻለን (አትክልት) ሊለውጠን ይከጀላል፡፡ እኛ ወደ ጌታችን ከጃዮች ነን፤» (አሉ)፡፡
  • 33. ቅጣቱ እንደዚሁ ነው፡፡ የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት ታላቅ ነው፡፡ የሚያውቁት በኾኑ ኖሮ (በተጠነቀቁ ነበር)፡፡
  • 34. ለጥንቁቆቹ በጌታቸው ዘንድ መጠቀሚያ ገነቶች አሏቸው፡፡
  • 35. ሙስሊሞቹን እንደ ከሓዲዎች እናደርጋለን?
  • 36. ለእናንተ ምን (አስረጅ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ፡፡
  • 37. በእውነቱ ለእናንተ በእርሱ የምታጠኑበት መጽሐፍ አላችሁን?
  • 38. በውስጡ ለእናንተ የምትመርጡት አላችሁ (የሚል)
  • 39. ወይስ ለእናንተ የምትፈርዱት አላችሁ በማለት (ቃል ኪዳን የገባንላችሁ) እስከ ትንሣኤ ቀን ደራሽ የኾኑ መሓላዎች ለእናንተ በእኛ ላይ አሏችሁን?
  • 40. በዚህ ማንኛቸው ተያያዥ እንደ ኾነ ጠይቃቸው፡፡
  • 41. ወይስ ለእነርሱ (በፍርዳቸው ተስማሚ) «ተጋሪዎች» አሏቸውን? እውነተኞችም እንደኾኑ «ተጋሪዎቻቸውን» ያምጡ፡፡
  • 42. ባት የሚገለጥበትን (ከሓዲዎች) ወደ መስገድም የሚጥጠሩበትንና የማይችሉበት ቀን (አስታውስ)፡፡
  • 43. ዓይኖቻቸው የፈሩ ውርደት የምትሸፍናቸው ሲኾኑ፤ (ወደ ስግደት የሚጠሩበትን)፤ እነርሱም (በምድረ ዓለም) ደህና ኾነው ሳሉ ወደ ስግደት በእርግጥ ይጠሩ ነበሩ፡፡
  • 44. በዚህም ንግግር ከሚያስተባብሉት ሰዎች ጋር ተዎኝ፡፡ (እነርሱን እኔ እበቃሃለሁ)፡፡ ከማያውቁት ስፍራ አዘናግተን እንይዛቸዋለን፡፡
  • 45. እነርሱንም አዘገያለሁ፡፡ ዘዴዬ ብርቱ ነውና፡፡
  • 46. በእውነቱ ዋጋን ትጠይቃቸዋለህን? ስለዚህ እነርሱ ከዕዳ የተከበዱ ናቸውን?
  • 47. ወይስ እነርሱ ዘንድ የሩቁ ምስጢር ዕውቀት አልለን? ስለዚህ እነርሱ ይጽፋሉን?
  • 48. ለጌታህም ፍርድ ታገሥ፤ (በመበሳጨትና ባለ መታገሥ) እንደ ዓሣው ባለቤትም (እንደ ዮናስ) አትኹን፡፡ እርሱ በጭንቀት የተመላ ኾኖ (ጌታውን) በተጣራ ጊዜ፡፡
  • 49. ከጌታው የኾነ ጸጋ ባላገኘው ኖሮ በምድረ በዳ ተወቃሽ ኾኖ በተጣለ ነበር፡፡
  • 50. ጌታውም (በነቢይነት) መረጠው፡፡ ከደጋጎቹም አደረገው፡፡
  • 51. እነሆ እነዚያም የካዱት ሰዎች ቁርኣኑን በሰሙ ጊዜ በዓይኖቻቸው ሊጥሉህ (ሊያጠፉህ) ይቀርባሉ፡፡ «እርሱም በእርግጥ ዕብድ ነው» ይላሉ፡፡
  • 52. ግን እርሱ (ቁርኣን) ለዓለማት መገሰጫ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡
ሼር ያድርጉ
logo
logo
logo
logo
logo
  • 1.ورَةُ الْفَاتِحَة
  • 2.ورَةُ البقرة
  • 3.سُورَةُ آل عمران
  • 4.سورة النساء
  • 5.سورۃ المائدة
  • 6.سورة الأنعام
  • 7.سورة الاعراف
  • 8.سورۃ الانفال
  • 9.سورة التوبة
  • 10.سورة يونس
  • 11.سورۃ ھود
  • 12.سورة يوسف
  • 13.سورة الرعد
  • 14.سورة ابراهيم
  • 15.سورة الحجر
  • 16.سورة النحل
  • 17.سورة الإسراء
  • 18.سورة الكهف
  • 19.سورة مريم
  • 20.سورة طه
  • 21.سورة الأنبياء
  • 22.سورة الحج
  • 23.سورة المؤمنون
  • 24.سورة النور
  • 25.سورة الفرقان
  • 26.سورة الشعراء
  • 27.سورة النمل
  • 28.سورة القصص
  • 29.سورة العنكبوت
  • 30.سورة الروم
  • 31.سورة لقمان
  • 32.سورة السجدة
  • 33.سورة الأحزاب
  • 34.سورة سبإ
  • 35.سورة فاطر
  • 36.سورةيس
  • 37.سورة الصافات
  • 38.سورة ص
  • 39.سورة الزمر
  • 40.سورة غافر
  • 41.سورة فصلت
  • 42.سورة الشورى
  • 43.سورة الزخرف
  • 44.سورة الدخان
  • 45.سورة الجاثية
  • 46.سورة الأحقاف
  • 47.سورة محمد
  • 48.سورة الفتح
  • 49.ورة الحجرات
  • 50.سورة ق
  • 51.سورة الذاريات
  • 52.سورة الطور
  • 53.سورة النجم
  • 54.سورة القمر
  • 55.سورة الرحمن
  • 56.سورة الواقعة
  • 57.سورة الحديد
  • 58.سورة المجادلة
  • 59.سورة الحشر
  • 60.سورة الممتحنة
  • 61.سورة الصف
  • 62.سورة الجمعة
  • 63.سورة المنافقون
  • 64.سورة التغابن
  • 65.سورة الطلاق
  • 66.سورة التحريم
  • 67.سورة الملك
  • 68.سورة القلم
  • 69.سورة الحاقة
  • 70.سورة المعارج
  • 71.سورة نوح
  • 72.سورة الجن
  • 73.سورة المزمل
  • 74.سورة المدثر
  • 75.سورة القيامة
  • 76.سورة الانسان
  • 77.سورة المرسلات
  • 78.سورة النبإ
  • 79.سورة النازعات
  • 80.سورة عبس
  • 81.سورة التكوير
  • 82.سورة الإنفطار
  • 83.سورة المطففين
  • 84.سورة الإنشقاق
  • 85.سورة البروج
  • 86.سورة الطارق
  • 87.سورة الأعلى
  • 88.سورة الغاشية
  • 89.سورة الفجر
  • 90.سورة البلد
  • 91.سورة الشمس
  • 92.سورة الليل
  • 93.سورة الضحى
  • 94.سورة الشرح
  • 95.سورة التين
  • 96.سورة العلق
  • 97.سورة القدر
  • 98.سورة البينة
  • 99.سورة الزلزلة
  • 100.سورة العاديات
  • 101.سورة القارعة
  • 102.Aسورة التكاثر
  • 103.سورة العصر
  • 104.سورة الهمزة
  • 105.سورة الفيل
  • 106.سورة قريش
  • 107.سورة الماعون
  • 108.سورة الكوثر
  • 109.سورة الكافرون
  • 110.سورة النصر
  • 111.سورة المسد
  • 112.سورة الإخلاص
  • 113.سورة الفلق
  • 114.سورة الناس