• 1. አንተ ነቢዩ ሆይ! ሴቶችን መፍታት ባሰባችሁ ጊዜ፤ ለዒዳቸው ፍቱዋቸው፡፡ ዒዳንም ቁጠሩ፡፡ አላህንም ጌታችሁን ፍሩ፡፡ ግልጽ የኾነችን ጠያፍ ካልሠሩ በስተቀር ከቤቶቻቸው አታውጡዋቸው፤ አይውጡም፡፡ ይህችም የአላህ ሕግጋት ናት፡፡ የአላህንም ሕግጋት የተላለፈ ሰው በእርግጥ ነፍሱን በደለ፡፡ ከዚህ (ፍች) በኋላ አላህ (የመማለስ) ነገርን ምናልባት ያመጣ እንደኾነ አታውቅም፡፡
  • 2. ጊዜያቸውንም ለመዳረስ በተቃረቡ ጊዜ በመልካም ያዙዋቸው፡፡ ወይም በመልካም ተለያዩዋቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ሁለት የትክክለኛነት ባለቤቶችን አስመስክሩ፡፡ ምስክርነትንም ለአላህ አስተካክሉ፡፡ ይህ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የኾነ ሰው ሁሉ በእርሱ ይገሰጽበታል፡፡ አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል፡፡
  • 3. ከማያስበውም በኩል ሲሳየን ይሰጠዋል፡፡ በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው፡፡ አላህ ፈቃዱን አድራሽ ነው፡፡ አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን በእርግጥ አድርጓል፡፡
  • 4. እኒያም ከሴቶቻቸው ከአደፍ ያቋረጡት (በዒዳቸው ሕግ) ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሦስት ወር ነው፡፡ እኒያም ገና አደፍን ያላዩት (ዒዳቸው እንደዚሁ ነው)፡፡ የእርግዝና ባለቤቶችም ጊዜያቸው እርጉዛቸውን መውለድ ነው፡፡ አላህንም የሚፈራ ሰው ከነገሩ ሁሉ ለርሱ መግራትን ያደርግለታል፡፡
  • 5. ይህ የአላህ ፍርድ ነው፡፡ ወደእናንተ አወረደው፡፡ አላህንም የሚፈራ ሰው ኀጢኣቶቹን ከእርሱ ይሰርይለታል፡፡ ምንዳንም ለእርሱ ያተልቅለታል፡፡
  • 6. ከችሎታችሁ ከተቀመጣችሁበት ስፍራ አስቀምጧቸው፡፡ በእነርሱም ላይ ልታጣብቡ አትጉዷቸው፡፡ የእርግዝና ባለቤቶችም ቢኾኑ እርጉዛቸውን እስኪወልዱ ድረስ በእነርሱ ላይ ቀልቡ፡፡ ለእናንተም (ልጆቻችሁን) ቢያጠቡላችሁ ምንዳዎቻቸውን ስጧቸው፡፡ በመካከላችሁም በመልካም ነገር ተመካከሩ፡፡ ብትቸጋገሩም ለእርሱ ሌላ (ሴት) ታጠባለታለች፡፡
  • 7. የችሎታ ባለቤት ከችሎታው ይቀልብ፡፡ በእርሱም ላይ ሲሳዩ የተጠበበበት ሰው አላህ ከሰጠው ይቀልብ አላህ ነፍስን የሰጣትን እንጅ አያስገድድም፡፡ አላህ ከችግር በኋላ ምቾትን በእርግጥ ያደርጋል፡፡
  • 8. ከከተማም ከጌታዋ ትዕዛዝ ከመልክተኞቹም ያመጸች፣ ብርቱንም ቁጥጥር የተቆጣጠርናት፣ መጥፎንም ቅጣት የቀጣናት ብዙ ናት፡፡
  • 9. የነገርዋንም ቅጣት ቀመሰች፡፡ የነገርዋም መጨረሻ ከሳራ ኾነ፡፡
  • 10. አላህ ለእነርሱ ብርቱን ቅጣት አዘጋጀ፡፡ እናንተም የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ እነዚያ ያመኑ (ሆይ)! አላህ ወደናንተ ግሳጼን በእርግጥ አወረደ፡፡ መልክተኛን (ላከ)፡፡
  • 11. እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣ ዘንድ የአላህን አንቀጾች ገላጮች ሲኾኑ በእናንተ ላይ የሚያነብላችሁን (ላከ)፡፡ በአላህም አንቀጾች የሚያምን፣ መልካምን ሥራ የሚሠራም ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈስሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲኾኑ ያገባዋል፡፡ አላህ ለእርሱ ሲሳይን በእርግጥ አሳመረ፡፡
  • 12. አላህ ያ ሰባትን ሰማያት የፈጠረ ነው፡፡ ከምድርም መሰላቸውን (ፈጥሮአል)፤ በመካከላቸው ትእዛዙ ይወርዳል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መኾኑን አላህም በነገሩ ሁሉ በዕውቀት ያካበበ መኾኑን በዕውቀት ያካበበ መኾኑን ታወቁ ዘንድ (ይህንን አሳወቃችሁ)፡፡
ሼር ያድርጉ
logo
logo
logo
logo
logo
  • 1.ورَةُ الْفَاتِحَة
  • 2.ورَةُ البقرة
  • 3.سُورَةُ آل عمران
  • 4.سورة النساء
  • 5.سورۃ المائدة
  • 6.سورة الأنعام
  • 7.سورة الاعراف
  • 8.سورۃ الانفال
  • 9.سورة التوبة
  • 10.سورة يونس
  • 11.سورۃ ھود
  • 12.سورة يوسف
  • 13.سورة الرعد
  • 14.سورة ابراهيم
  • 15.سورة الحجر
  • 16.سورة النحل
  • 17.سورة الإسراء
  • 18.سورة الكهف
  • 19.سورة مريم
  • 20.سورة طه
  • 21.سورة الأنبياء
  • 22.سورة الحج
  • 23.سورة المؤمنون
  • 24.سورة النور
  • 25.سورة الفرقان
  • 26.سورة الشعراء
  • 27.سورة النمل
  • 28.سورة القصص
  • 29.سورة العنكبوت
  • 30.سورة الروم
  • 31.سورة لقمان
  • 32.سورة السجدة
  • 33.سورة الأحزاب
  • 34.سورة سبإ
  • 35.سورة فاطر
  • 36.سورةيس
  • 37.سورة الصافات
  • 38.سورة ص
  • 39.سورة الزمر
  • 40.سورة غافر
  • 41.سورة فصلت
  • 42.سورة الشورى
  • 43.سورة الزخرف
  • 44.سورة الدخان
  • 45.سورة الجاثية
  • 46.سورة الأحقاف
  • 47.سورة محمد
  • 48.سورة الفتح
  • 49.ورة الحجرات
  • 50.سورة ق
  • 51.سورة الذاريات
  • 52.سورة الطور
  • 53.سورة النجم
  • 54.سورة القمر
  • 55.سورة الرحمن
  • 56.سورة الواقعة
  • 57.سورة الحديد
  • 58.سورة المجادلة
  • 59.سورة الحشر
  • 60.سورة الممتحنة
  • 61.سورة الصف
  • 62.سورة الجمعة
  • 63.سورة المنافقون
  • 64.سورة التغابن
  • 65.سورة الطلاق
  • 66.سورة التحريم
  • 67.سورة الملك
  • 68.سورة القلم
  • 69.سورة الحاقة
  • 70.سورة المعارج
  • 71.سورة نوح
  • 72.سورة الجن
  • 73.سورة المزمل
  • 74.سورة المدثر
  • 75.سورة القيامة
  • 76.سورة الانسان
  • 77.سورة المرسلات
  • 78.سورة النبإ
  • 79.سورة النازعات
  • 80.سورة عبس
  • 81.سورة التكوير
  • 82.سورة الإنفطار
  • 83.سورة المطففين
  • 84.سورة الإنشقاق
  • 85.سورة البروج
  • 86.سورة الطارق
  • 87.سورة الأعلى
  • 88.سورة الغاشية
  • 89.سورة الفجر
  • 90.سورة البلد
  • 91.سورة الشمس
  • 92.سورة الليل
  • 93.سورة الضحى
  • 94.سورة الشرح
  • 95.سورة التين
  • 96.سورة العلق
  • 97.سورة القدر
  • 98.سورة البينة
  • 99.سورة الزلزلة
  • 100.سورة العاديات
  • 101.سورة القارعة
  • 102.Aسورة التكاثر
  • 103.سورة العصر
  • 104.سورة الهمزة
  • 105.سورة الفيل
  • 106.سورة قريش
  • 107.سورة الماعون
  • 108.سورة الكوثر
  • 109.سورة الكافرون
  • 110.سورة النصر
  • 111.سورة المسد
  • 112.سورة الإخلاص
  • 113.سورة الفلق
  • 114.سورة الناس