• 1. በኮከብ እምላለሁ በወደቀ (በገባ) ጊዜ፡፡
  • 2. ነቢያችሁ (ሙሐመድ) አልተሳሳተም፤ አልጠመመምም፡፡
  • 3. ከልብ ወለድም አይናገርም፡፡
  • 4. እርሱ (ንግግሩ) የሚወርረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡
  • 5. ኀይሎቹ ብርቱው (መልአክ) አስተማረው፡፡
  • 6. የዕውቀት ባለቤት የኾነው (አስተማረው፤ በተፈጥሮ ቅርጹ ኾኖ በአየር ላይ) ተደላደለም፡፡
  • 7. እርሱ በላይኛው አድማስ ኾኖ፡፡
  • 8. ከዚያም ቀረበ፤ ወረደም፡፡
  • 9. (ከእርሱ) የሁለት ደጋኖች ጫፍ ያህል ወይም (ከዚህ) ይበልጥ የቀረበ ኾነም፡፡
  • 10. ወደ ባሪያውም (አላህ) ያወረደውን አወረደ፡፡
  • 11. (ነቢዩም በዓይኑ) ያየውን ልቡ አልዋሸም፡፡
  • 12. ታዲያ በሚያየው ላይ ትከራከሩታላችሁን?
  • 13. በሌላይቱም መውረድ ጊዜ በእርግጥ አይቶታል፡፡
  • 14. በመጨረሻይቱ ቁርቁራ አጠገብ፤
  • 15. እርሷ ዘንድ መኖሪያይቱ ገነት ያለች ስትኾን፡፡
  • 16. ቁርቁራይቱን የሚሸፍን ነገር በሚሸፍናት ጊዜ (አየው)፡፡
  • 17. ዓይኑ (ካየው) አልተዘነበለም፡፡ ወሰንም አላለፈም፡፡
  • 18. ከጌታው ታምራቶች ታላላቆቹን በእርግጥ አየ፡፡
  • 19. አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን?
  • 20. ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን (አያችሁን? የምትግገዟቸው ኃይል አላቸውን?)
  • 21. ለእናንተ ወንድ ለእርሱም ሴት (ልጅ) ይኖራልን?
  • 22. ይህቺ ያን ጊዜ አድላዊ ክፍያ ናት፡፡
  • 23. እነርሱ እናንተና አባቶቻችሁ (አማልክት ብላችሁ) የጠራችኋቸው ስሞች ብቻ እንጅ ምንም አይደሉም፡፡ አላህ በእርሷ (መግገዛት) ምንም ማስረጃ አላወረደም፡፡ ከጌታቸውም መምሪያ የመጣላቸው ሲኾኑ ጥርጣሬንና ነፍሶች የሚዘነበሉበትን እንጅ ሌላ አይከተሉም፡፡
  • 24. ለሰው የተመኘው ሁሉ አለውን?
  • 25. መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም (ዓለም) የአላህ ብቻ ናቸው፡፡
  • 26. በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች (ሊማለዱለት) ለሚሻውና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም፡፡
  • 27. እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት መላእክትን በሴት አጠራር ይጠራሉ፡፡
  • 28. ለእነርሱም በእርሱ ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ ጥርጣሬን እንጅ ሌላን አይከተሉም፡፡ ጥርጣሬም ከእውነት ምንም አያብቃቃም፡፡
  • 29. ከግሣጼያችንም (ከቁርኣን) ከሸሸና አነስተኛይቱን ሕይወት እንጅ ሌላን ከማይሻ ሰው ዙር (ተወው)፡፡
  • 30. ይህ (አነስተኛይቱን ሕይወት መምረጥ) ከዕውቀት ድካቸው ነው፡፡ ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን በእርግጥ ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም የቀናውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡
  • 31. በሰማያት ያለውና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ እነዚያን ያጠፉትን በሠሩት ሊቀጣ እነዚያን ያሳመሩትንም በመልካሚቱ (ገነት) ሊመነዳ (የጠመመውንና የቀናውን ያውቃል)፡፡
  • 32. (እነርሱ) እነዚያ የኃጢኣትን ታላለቆችና አስጸያፊዎቹን የሚርቁ ናቸው፡፡ ግን ትናንሾቹ የሚማሩ ናቸው፡፡ ጌታህ ምሕረተ ሰፊ ነውና፡፡ ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜ እናንተም በእናቶቻችሁ ሆዶች ውስጥ ሽሎች በኾናችሁ ጊዜ እርሱ በናንተ (ኹነታ) ዐዋቂ ነው፡፡ ነፍሶቻችሁንም አታወድሱ እርሱ የሚፈራውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡
  • 33. ያንን (ከእምነት) የዞረውን አየህን?
  • 34. ጥቂትን የሰጠውንና ያቋረጠውንም (አየህን?)
  • 35. የሩቁ ምስጢር ዕውቀት እርሱ ዘንድ አልለን? ስለዚህ እርሱ ያያልን?
  • 36. ይልቁንም በዚያ በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ ባለው ነገር አልተነገረምን?
  • 37. በዚያም (የታዘዘውን) በፈጸመው በኢብራሂም (ጽሑፎች ውስጥ ባለው አልተነገረምን?)
  • 38. (እርሱም ኃጢያት) ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢኣት አትሸከምም፡፡
  • 39. ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም፡፡
  • 40. ሥራውም ሁሉ ወደ ፊት ይታያል፡፡
  • 41. ከዚያም ሙሉውን ምንዳ ይመነዳዋል፡፡
  • 42. መጨረሻውም ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡
  • 43. እነሆ እርሱም አስሳቀ፣ አስለቀሰም፡፡
  • 44. እነሆ እርሱም ገደለ፣ አስነሳም፡፡
  • 45. እርሱም ሁለቱን ዓይነቶች ወንድንና ሴትን ፈጠረ፡፡
  • 46. ከፍትወት ጠብታ (በማህጸን ውስጥ) በምትፈሰስ ጊዜ፡፡
  • 47. የኋለኛይቱም ማስነሳት በእርሱ ላይ ነው፡፡
  • 48. እነሆ እርሱም አከበረ፣ ጥሪተኛም አደረገ፡፡
  • 49. እነሆ እርሱም የሺዕራ ጌታ ነው፡፡
  • 50. እነሆ እርሱም የፊተኛይቱን ዓድ አጥፍቷል፡፡
  • 51. ሰሙድንም (አጥፍቷል)፤ አላስቀረምም፡፡
  • 52. በፊትም የኑሕን ሕዝቦች (አጥፍቷል)፡፡ እነርሱ በጣም በደለኞችና እጅግ የጠመሙ እነርሱ ነበሩና፡፡
  • 53. የተገለበጠችውንም ከተማ ደፋ፡፡
  • 54. ያለበሳትንም አለበሳት፡፡
  • 55. ከጌታህም ጸጋዎች በየትኛው ትጠራጠራለህ?
  • 56. ይህ ከፊተኞቹ አስፈራሪዎች (ጎሳ) የኾነ አስፈራሪ ነው፡፡
  • 57. ቀራቢይቱ (ኅልፈተ ዓለም) ቀረበች፡፡
  • 58. ለእርሷ ከአላህ ሌላ ገላጭ የላትም፡፡
  • 59. ከዚህ ንግግር ትደነቃላችሁን?
  • 60. ትስቃላችሁምን? አታለቅሱምን?
  • 61. እናንተም ዘንጊዎች ናችሁ፡፡
  • 62. ለአላህም ስገዱ ተገዙትም፡፡
ሼር ያድርጉ
logo
logo
logo
logo
logo
  • 1.ورَةُ الْفَاتِحَة
  • 2.ورَةُ البقرة
  • 3.سُورَةُ آل عمران
  • 4.سورة النساء
  • 5.سورۃ المائدة
  • 6.سورة الأنعام
  • 7.سورة الاعراف
  • 8.سورۃ الانفال
  • 9.سورة التوبة
  • 10.سورة يونس
  • 11.سورۃ ھود
  • 12.سورة يوسف
  • 13.سورة الرعد
  • 14.سورة ابراهيم
  • 15.سورة الحجر
  • 16.سورة النحل
  • 17.سورة الإسراء
  • 18.سورة الكهف
  • 19.سورة مريم
  • 20.سورة طه
  • 21.سورة الأنبياء
  • 22.سورة الحج
  • 23.سورة المؤمنون
  • 24.سورة النور
  • 25.سورة الفرقان
  • 26.سورة الشعراء
  • 27.سورة النمل
  • 28.سورة القصص
  • 29.سورة العنكبوت
  • 30.سورة الروم
  • 31.سورة لقمان
  • 32.سورة السجدة
  • 33.سورة الأحزاب
  • 34.سورة سبإ
  • 35.سورة فاطر
  • 36.سورةيس
  • 37.سورة الصافات
  • 38.سورة ص
  • 39.سورة الزمر
  • 40.سورة غافر
  • 41.سورة فصلت
  • 42.سورة الشورى
  • 43.سورة الزخرف
  • 44.سورة الدخان
  • 45.سورة الجاثية
  • 46.سورة الأحقاف
  • 47.سورة محمد
  • 48.سورة الفتح
  • 49.ورة الحجرات
  • 50.سورة ق
  • 51.سورة الذاريات
  • 52.سورة الطور
  • 53.سورة النجم
  • 54.سورة القمر
  • 55.سورة الرحمن
  • 56.سورة الواقعة
  • 57.سورة الحديد
  • 58.سورة المجادلة
  • 59.سورة الحشر
  • 60.سورة الممتحنة
  • 61.سورة الصف
  • 62.سورة الجمعة
  • 63.سورة المنافقون
  • 64.سورة التغابن
  • 65.سورة الطلاق
  • 66.سورة التحريم
  • 67.سورة الملك
  • 68.سورة القلم
  • 69.سورة الحاقة
  • 70.سورة المعارج
  • 71.سورة نوح
  • 72.سورة الجن
  • 73.سورة المزمل
  • 74.سورة المدثر
  • 75.سورة القيامة
  • 76.سورة الانسان
  • 77.سورة المرسلات
  • 78.سورة النبإ
  • 79.سورة النازعات
  • 80.سورة عبس
  • 81.سورة التكوير
  • 82.سورة الإنفطار
  • 83.سورة المطففين
  • 84.سورة الإنشقاق
  • 85.سورة البروج
  • 86.سورة الطارق
  • 87.سورة الأعلى
  • 88.سورة الغاشية
  • 89.سورة الفجر
  • 90.سورة البلد
  • 91.سورة الشمس
  • 92.سورة الليل
  • 93.سورة الضحى
  • 94.سورة الشرح
  • 95.سورة التين
  • 96.سورة العلق
  • 97.سورة القدر
  • 98.سورة البينة
  • 99.سورة الزلزلة
  • 100.سورة العاديات
  • 101.سورة القارعة
  • 102.Aسورة التكاثر
  • 103.سورة العصر
  • 104.سورة الهمزة
  • 105.سورة الفيل
  • 106.سورة قريش
  • 107.سورة الماعون
  • 108.سورة الكوثر
  • 109.سورة الكافرون
  • 110.سورة النصر
  • 111.سورة المسد
  • 112.سورة الإخلاص
  • 113.سورة الفلق
  • 114.سورة الناس