• 1. ሐ.መ (ሓ ሚም)፡፡
  • 2. አብራሪ በኾነው መጽሐፍ እንምላለን፡፡
  • 3. እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው፡፡ እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና፡፡
  • 4. በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል፡፡
  • 5. ከእኛ ዘንድ የኾነ ትእዛዝ ሲኾን (አወረድነው)፡፡ እኛ (መልክተኞችን) ላኪዎች ነበርን፡፡
  • 6. ከጌታህ በኾነው ችሮታ (ተላኩ)፡፡ እነሆ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡
  • 7. የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ነገር ሁሉ ጌታ ከኾነው (ተላኩ)፡፡ የምታረጋግጡ እንደኾናችሁ (ነገሩ እንዳልነው መኾኑን እወቁ)፡፡
  • 8. ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ያደርጋል፡፡ ይገድላልም፡፡ ጌታችሁ የመጀመሪያዎቹ አባቶቻችሁም ጌታ ነው፡፡
  • 9. በእውነቱ እነርሱ የሚጫወቱ ሲኾኑ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡
  • 10. ሰማይም በግልጽ ጭስ የምትመጣበትን ቀን ተጠባበቅ፡፡
  • 11. ሰዎችን የሚሸፍን (በኾነ ጭስ) ይህ አሳማሚ ቅጣት ነው፡፡
  • 12. «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ላይ ቅጣቱን ግለጥልን፡፡ እኛ አማኞች እንኾናለንና» (ይላሉም)፡፡
  • 13. (ቅጣቱ በወረደ ጊዜ) ለእነርሱ መግገሰጽ እንዴት ይኖራቸዋል? አስረጅ መልክተኛ የመጣቸው ሲኾን (የካዱም ሲኾኑ)፡፡
  • 14. ከዚያም ከእርሱ የዞሩ፤ (ከሰው) «የተሰተማረ ዕብድ ነው» ያሉም ሲኾኑ፡፡
  • 15. እኛ ቅጣቱን ለጥቂት ጊዜ ገላጮች ነን፡፡ እናንተ (ወደ ክህደታችሁ) በእርግጥ ተመላሾች ናችሁ፡፡
  • 16. ታላቂቱን ብርቱ አያያዝ በምንይዝበት ቀን፤ እኛ ተበቃዮች ነን፡፡
  • 17. ከእነርሱም በፊት የፈርዖንን ሕዝቦች በእርግጥ ሞከርን፡፡ ክቡር መልእክተኛም መጣላቸው፡፡
  • 18. «የአላህን ባሮች ወደኔ አድርሱ፡፡ እኔ ለእናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝና፡፡
  • 19. «በአላህም ላይ አትኩሩ፡፡ እኔ ግልጽ የኾነን አስረጅ ያመጣሁላችሁ ነኝና (በማለት መጣላቸው)፡፡
  • 20. «እኔም እንዳትወግሩኝ በጌታየና በጌታችሁ ተጠብቂያለሁ፡፡
  • 21. «በእኔም ባታምኑ ራቁኝ» (ተዉኝ አለ)፡፡
  • 22. ቀጥሎም (ስለ ዛቱበት) «እነዚህ አመጸኞች ሕዝቦች ናቸው» (አጥፋቸው) ሲል ጌታውን ለመነ፡፡
  • 23. (ጌታው) «ባሮቼንም ይዘህ በሌሊት ኺድ፡፡ እናንተ የሚከተሉዋችሁ ናችሁና፡፡
  • 24. «ባሕሩንም የተከፈተ ኾኖ ተወው፡፡ እነርሱ የሚሰጥጠሙ ሰራዊት ናቸውና» (አለው)፡፡
  • 25. ከአትክልቶችና ከምንጮችም ብዙ ነገሮችን ተዉ፡፡
  • 26. ከአዝመራዎችም ከመልካም መቀመጫም፡፡
  • 27. በእርሷ ተደሳቾች ከነበሩባትም ድሎት (ብዙን ነገር ተዉ)፡፡
  • 28. (ነገሩ) እንደዚሁ ኾነ፡፡ ሌሎችንም ሕዝቦች አወረስናት፡፡
  • 29. ሰማይና ምድርም በእነርሱ ላይ አላለቀሱም፡፡ የሚቆዩም አልነበሩም፡፡
  • 30. የእስራኤልንም ልጆች አዋራጅ ከኾነ ስቃይ በእርግጥ አዳንናቸው፡፡
  • 31. ከፈርዖን፤ እርሱ የኮራ ከወሰን አላፊዎቹ ነበርና፡፡
  • 32. ከማወቅም ጋር በዓለማት ላይ በእርግጥ መረጥናቸው፡፡
  • 33. ከታምራቶችም በውስጡ ግልጽ የኾነ ፈተና ያለበትን ሰጠናቸው፡፡
  • 34. እነዚህ (የመካ ከሓዲዎች) በእርግጥ ይላሉ፡-
  • 35. እርሷ የፊተኛይቱ ሞታችን እንጅ አይደለችም፡፡ እኛም የምንቀሰቀስ አይደለንም፡፡
  • 36. እውነተኞችም እንደ ኾናችሁ አባቶቻችንን አምጡልን፡፡
  • 37. እነርሱ በላጮች ናቸውን ወይስ የቱብበዕ ሕዝቦችና እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት? አጠፋናቸው፡፡ እነርሱ አመጸኞች ነበሩና፡፡
  • 38. ሰማያትንና ምድርንም በሁለቱ መካከል ያለውንም ሁሉ ቀላጆች ኾነን አልፈጠርንም፡፡
  • 39. ሁለቱንም በምር እንጅ አልፈጠርናቸውም፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡
  • 40. የመለያው ቀን ለሁሉም ቀጠሯቸው ነው፡፡
  • 41. ዘመድ ከዘመዱ ምንንም የማይጠቅምበት እነርሱም የማይርረዱበት ቀን ነው፡፡
  • 42. አላህ ያዘነለት ሰውና ያመነ ብቻ ሲቀር፡፡ (እርሱስ ይርረዳል)፡፡ እርሱ አሸናፊው አዛኙ ነውና፡፡
  • 43. የዘቁመ ዛፍ
  • 44. የኀጢኣተኛው ምግብ ነው፡፡
  • 45. እንደ ዘይት አተላ ነው፡፡ በሆዶች ውስጥ የሚፈላ ሲኾን፡፡
  • 46. እንደ ገነፈለ ውሃ አፈላል (የሚፈላ ሲኾን)፡፡
  • 47. ያዙት፤ ወደ ገሀነም መካከልም በኀይል ጎትቱት፡፡
  • 48. ከዚያም «ከራሱ በላይ ከፈላ ውሃ ስቃይ አንቧቡበት፡፡»
  • 49. «ቅመስ፤ አንተ አሸናፊው ክብሩ ነህና» (ይባላል)፡፡
  • 50. «ይህ ያ በእርሱ ትጠራጠሩበት የነበራችሁት ነው» (ይባላሉ)፡፡
  • 51. ጥንቁቆቹ በእርግጥ በጸጥተኛ መኖሪያ ውስጥ ናቸው፡፡
  • 52. በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡
  • 53. ፊት ለፊት የተቅጣጩ ኾነው ከስስ ሐርና ከወፍራም ሐር ይለብሳሉ፡፡
  • 54. (ነገሩ) እንደዚሁ ነው፤ ዓይናማዎች የኾኑን ነጫጭ ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን፡፡
  • 55. በእርሷም ውስጥ የተማመኑ ኾነው፤ ከፍራፍሬ ሁሉ ያዝዛሉ፡፡
  • 56. የፊተኛይቱን ሞት እንጅ (ዳግመኛ) በእርሷ ውስጥ ሞትን አይቀምሱም፡፡ የገሀነምንም ቅጣት (አላህ) ጠበቃቸው፡፡
  • 57. ከጌታህ በኾነ ችሮታ (ጠበቃቸው)፡፡ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡
  • 58. (ቁርኣኑን) በቋንቋህም ያገራነው (ሕዝቦችህ) ይገነዘቡ ዘንድ ብቻ ነው፡፡
  • 59. ተጠባበቅም እነርሱ ተጠባባቂዎች ናቸውና፡፡
ሼር ያድርጉ
logo
logo
logo
logo
logo
  • 1.ورَةُ الْفَاتِحَة
  • 2.ورَةُ البقرة
  • 3.سُورَةُ آل عمران
  • 4.سورة النساء
  • 5.سورۃ المائدة
  • 6.سورة الأنعام
  • 7.سورة الاعراف
  • 8.سورۃ الانفال
  • 9.سورة التوبة
  • 10.سورة يونس
  • 11.سورۃ ھود
  • 12.سورة يوسف
  • 13.سورة الرعد
  • 14.سورة ابراهيم
  • 15.سورة الحجر
  • 16.سورة النحل
  • 17.سورة الإسراء
  • 18.سورة الكهف
  • 19.سورة مريم
  • 20.سورة طه
  • 21.سورة الأنبياء
  • 22.سورة الحج
  • 23.سورة المؤمنون
  • 24.سورة النور
  • 25.سورة الفرقان
  • 26.سورة الشعراء
  • 27.سورة النمل
  • 28.سورة القصص
  • 29.سورة العنكبوت
  • 30.سورة الروم
  • 31.سورة لقمان
  • 32.سورة السجدة
  • 33.سورة الأحزاب
  • 34.سورة سبإ
  • 35.سورة فاطر
  • 36.سورةيس
  • 37.سورة الصافات
  • 38.سورة ص
  • 39.سورة الزمر
  • 40.سورة غافر
  • 41.سورة فصلت
  • 42.سورة الشورى
  • 43.سورة الزخرف
  • 44.سورة الدخان
  • 45.سورة الجاثية
  • 46.سورة الأحقاف
  • 47.سورة محمد
  • 48.سورة الفتح
  • 49.ورة الحجرات
  • 50.سورة ق
  • 51.سورة الذاريات
  • 52.سورة الطور
  • 53.سورة النجم
  • 54.سورة القمر
  • 55.سورة الرحمن
  • 56.سورة الواقعة
  • 57.سورة الحديد
  • 58.سورة المجادلة
  • 59.سورة الحشر
  • 60.سورة الممتحنة
  • 61.سورة الصف
  • 62.سورة الجمعة
  • 63.سورة المنافقون
  • 64.سورة التغابن
  • 65.سورة الطلاق
  • 66.سورة التحريم
  • 67.سورة الملك
  • 68.سورة القلم
  • 69.سورة الحاقة
  • 70.سورة المعارج
  • 71.سورة نوح
  • 72.سورة الجن
  • 73.سورة المزمل
  • 74.سورة المدثر
  • 75.سورة القيامة
  • 76.سورة الانسان
  • 77.سورة المرسلات
  • 78.سورة النبإ
  • 79.سورة النازعات
  • 80.سورة عبس
  • 81.سورة التكوير
  • 82.سورة الإنفطار
  • 83.سورة المطففين
  • 84.سورة الإنشقاق
  • 85.سورة البروج
  • 86.سورة الطارق
  • 87.سورة الأعلى
  • 88.سورة الغاشية
  • 89.سورة الفجر
  • 90.سورة البلد
  • 91.سورة الشمس
  • 92.سورة الليل
  • 93.سورة الضحى
  • 94.سورة الشرح
  • 95.سورة التين
  • 96.سورة العلق
  • 97.سورة القدر
  • 98.سورة البينة
  • 99.سورة الزلزلة
  • 100.سورة العاديات
  • 101.سورة القارعة
  • 102.Aسورة التكاثر
  • 103.سورة العصر
  • 104.سورة الهمزة
  • 105.سورة الفيل
  • 106.سورة قريش
  • 107.سورة الماعون
  • 108.سورة الكوثر
  • 109.سورة الكافرون
  • 110.سورة النصر
  • 111.سورة المسد
  • 112.سورة الإخلاص
  • 113.سورة الفلق
  • 114.سورة الناس