• 1. አ.ለ.መ (አሊፍ ላም ሚም)፡፡
  • 2. የመጽሐፉ መወረድ ጥርጥር የለበትም፡፡ ከዓለማት ጌታ ነው፡፡
  • 3. ይልቁንም «ቀጠፈው» ይላሉን? አይደለም፡፡ እርሱ ከጌታህ ዘንድ የሆነ እውነት ነው፡፡ በእርሱ ከአንተ በፊት ከአስፈራሪ (ነቢይ) ያልመጣባቸውን ሕዝቦች ልታስፈራራበት (ያወረደልህ ነው)፡፡ እነርሱ ሊምመሩ ይከጀላልና፡፡
  • 4. አላህ ያ ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸውም ያለውን ሁሉ በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ ከዚያም በዐርሹ ላይ (ስልጣኑ) የተደላደለ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳትም አማላጅም ምንም የላችሁም፤ አትገሰጹምን?
  • 5. ነገሩን ሁሉ ከሰማይ ወደ ምድር ያዘጋጃል፡፡ ከዚያም ከምትቆጥሩት (ዘመን) ልኩ ሺህ ዓመት በሆነ ቀን ውስጥ ወደርሱ ይወጣል (ይመለሳል)፡፡
  • 6. ይህ (ይህንን የሠራው) ሩቁንም ቅርቡንም ሁሉ ዐዋቂው አሸናፊው፣ አዛኙ (ጌታ) ነው፡፡
  • 7. ያ የፈጠረውን ነገር ሁሉ ያሳመረው የሰውንም ፍጥረት ከጭቃ የጀመረው ነው፡፡
  • 8. ከዚያም ዘሮቹን ከተንጣለለ፣ ከደካማ ውሃ ያደረገ ነው፡፡
  • 9. ከዚያም (ቅርጹን) አስተካከለው፡፡ በእርሱ ውስጥም ከመንፈሱ ነፋበት፤ (ነፍስ ዘራበት)፡፡ ለእናንተም ጆሮዎችን፣ ዓይኖችንና ልቦችንም አደረገላችሁ፡፡ በጣም ጥቂትን ብቻ ታመሰግናላችሁ፡፡
  • 10. «በምድርም ውስጥ (በስብሰን) በጠፋን ጊዜ እኛ በአዲስ መፈጠር ውስጥ እንሆናለን?» አሉ፡፡ በእውነቱ እነርሱ በጌታቸው መገናኘት ከሓዲዎች ናቸው፡፡
  • 11. «በእናንተ የተወከለው መልአከ ሞት ይገድላችኋል፡፡ ከዚያም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ» በላቸው፡፡
  • 12. አመጸኞችም በጌታቸው ዘንድ ራሶቻቸውን ያቀረቀሩ ሆነው «ጌታችን ሆይ! አየን፣ ሰማንም፡፡ መልካምን እንሠራለንና (ወደ ምድረ ዓለም) መልሰን፡፡ እኛ አረጋጋጮች ነን፡፡» (የሚሉ ሲሆኑ) ብታይ ኖሮ (አስደንጋጭን ነገር ታይ ነበር)፡፡
  • 13. በሻንም ኖሮ ነፍስን ሁሉ ቅንነቷን (እምነቷን) በሰጠናት ነበር፡፡ ግን ገሀነምን ከአጋንንትና ከሰዎች የተሰበሰቡ ሆነው በእርግጥ እሞላለሁ ማለት ቃሉ ከእኔ ተረጋግጧል፡፡
  • 14. ይህንንም ቀናችሁን መገናኘትን በመርሳታችሁ ምክንያት (ቅጣትን) ቅመሱ! እኛ ተውናችሁ፡፡ ትሠሩት በነበራችሁትም ጥፋት ዘውታሪን ቅጣት ቅመሱ (ይባላሉ)፡፡
  • 15. በአንቀጾቻችን የሚያምኑት እነዚያ በእርሷ በተገሰጹ ጊዜ ሰጋጆች ሆነው የሚወድቁትና እነርሱም የማይኮሩ ሆነው በጌታቸው ምስጋና (ተጎናጽፈው) የሚያወድሱት ብቻ ናቸው፡፡
  • 16. ጌታቸውን ለመፍራትና ለመከጀል የሚጠሩት ሆነው ጎኖቻቸው ከመጋደሚያ ስፍራዎች ይራራቃሉ፡፡ ከሰጠናቸውም (ጸጋ) ይለገሳሉ፡፡
  • 17. ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን (ጸጋ) ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም፡፡
  • 18. አማኝ የሆነ ሰው አመጸኛ እንደ ሆነ ሰው ነውን? አይስተካከሉም፡፡
  • 19. እነዚያ ያመኑና መልካሞችን የሰሩማ ለእነርሱ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት መስተንግዶ ሲሆኑ መኖሪያ ገነቶች አሏቸው፡፡
  • 20. እነዚያ ያመጹትማ፤ መኖሪያቸው እሳት ናት፡፡ ከእርሷ መውጣትን በፈለጉ ቁጥር በእርሷ ውስጥ ይመለሳሉ፡፡ ለእነርሱም «ያንን በእርሱ ታስተባብሉበት የነበራችሁትን የእሳት ቅጣት ቅመሱ» ይባላሉ፡፡
  • 21. ይመለሱ ዘንድም ከትልቁ ቅጣት በፊት (በዚህ ዓለም) ከትንሹ ቅጣት በእርግጥ እናቀምሳቸዋለን፡፡
  • 22. በጌታውም አንቀጾች ከተገሰጸና ከዚያም ከተዋት ሰው ይበልጥ በደለኛ ማነው? (የለም)፤ እኛ ከተንኮለኞቹ ተበቃዮች ነን፡፡
  • 23. ሙሳንም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ እርሱን ከመገናኘትህም በመጠራጠር ውስጥ አትሁን፡፡ ለእስራኤል ልጆችም መሪ አደረግነው፡፡
  • 24. በታገሱና በተዓምራቶቻችን የሚያረጋግጡ በሆኑም ጊዜ ከእነርሱ በትዕዛዛችን የሚመሩ መሪዎች አደረግን፡፡
  • 25. ጌታህ እርሱ በዚያ በእርሱ ይለያዩበት በነበሩት ነገር በትንሣኤ ቀን በመካከላቸው (በፍርድ) ይለያል፡፡
  • 26. ከክፍለ ዘመናት ሰዎች ብዙዎችን ያጠፋን መሆናችን በመኖሪያዎቻቸው የሚሄዱ ሲሆኑ ለእነርሱ አልተገለፀላቸውምን? በዚህ ውስጥ ምልክቶች አሉት፤ አይሰሙምን?
  • 27. እኛ ውሃን ወደ ደረቅ ምድር የምንነዳ እንስሶቻቸውና ነፍሶቻቸው ከእርሱ የሚበሉለትንም አዝመራ በእርሱ የምናወጣ መኾናችንን አያዩምን? አይመለከቱምን?
  • 28. «ከእውነተኞችም እንደሆናችሁ ይህ ፍርድ መቼ ነው?» ይላሉ፡፡
  • 29. «በፍርድ ቀን እነዚያን የካዱትን ሰዎች እምነታቸው አይጠቅማቸውም፡፡ እነርሱም ጊዜን አይሰጡም፤» በላቸው፡፡
  • 30. እነርሱንም ተዋቸው፡፡ ተጠባበቅም፤ እነርሱ ተጠባባቂዎች ናቸውና፡፡
ሼር ያድርጉ
logo
logo
logo
logo
logo
  • 1.ورَةُ الْفَاتِحَة
  • 2.ورَةُ البقرة
  • 3.سُورَةُ آل عمران
  • 4.سورة النساء
  • 5.سورۃ المائدة
  • 6.سورة الأنعام
  • 7.سورة الاعراف
  • 8.سورۃ الانفال
  • 9.سورة التوبة
  • 10.سورة يونس
  • 11.سورۃ ھود
  • 12.سورة يوسف
  • 13.سورة الرعد
  • 14.سورة ابراهيم
  • 15.سورة الحجر
  • 16.سورة النحل
  • 17.سورة الإسراء
  • 18.سورة الكهف
  • 19.سورة مريم
  • 20.سورة طه
  • 21.سورة الأنبياء
  • 22.سورة الحج
  • 23.سورة المؤمنون
  • 24.سورة النور
  • 25.سورة الفرقان
  • 26.سورة الشعراء
  • 27.سورة النمل
  • 28.سورة القصص
  • 29.سورة العنكبوت
  • 30.سورة الروم
  • 31.سورة لقمان
  • 32.سورة السجدة
  • 33.سورة الأحزاب
  • 34.سورة سبإ
  • 35.سورة فاطر
  • 36.سورةيس
  • 37.سورة الصافات
  • 38.سورة ص
  • 39.سورة الزمر
  • 40.سورة غافر
  • 41.سورة فصلت
  • 42.سورة الشورى
  • 43.سورة الزخرف
  • 44.سورة الدخان
  • 45.سورة الجاثية
  • 46.سورة الأحقاف
  • 47.سورة محمد
  • 48.سورة الفتح
  • 49.ورة الحجرات
  • 50.سورة ق
  • 51.سورة الذاريات
  • 52.سورة الطور
  • 53.سورة النجم
  • 54.سورة القمر
  • 55.سورة الرحمن
  • 56.سورة الواقعة
  • 57.سورة الحديد
  • 58.سورة المجادلة
  • 59.سورة الحشر
  • 60.سورة الممتحنة
  • 61.سورة الصف
  • 62.سورة الجمعة
  • 63.سورة المنافقون
  • 64.سورة التغابن
  • 65.سورة الطلاق
  • 66.سورة التحريم
  • 67.سورة الملك
  • 68.سورة القلم
  • 69.سورة الحاقة
  • 70.سورة المعارج
  • 71.سورة نوح
  • 72.سورة الجن
  • 73.سورة المزمل
  • 74.سورة المدثر
  • 75.سورة القيامة
  • 76.سورة الانسان
  • 77.سورة المرسلات
  • 78.سورة النبإ
  • 79.سورة النازعات
  • 80.سورة عبس
  • 81.سورة التكوير
  • 82.سورة الإنفطار
  • 83.سورة المطففين
  • 84.سورة الإنشقاق
  • 85.سورة البروج
  • 86.سورة الطارق
  • 87.سورة الأعلى
  • 88.سورة الغاشية
  • 89.سورة الفجر
  • 90.سورة البلد
  • 91.سورة الشمس
  • 92.سورة الليل
  • 93.سورة الضحى
  • 94.سورة الشرح
  • 95.سورة التين
  • 96.سورة العلق
  • 97.سورة القدر
  • 98.سورة البينة
  • 99.سورة الزلزلة
  • 100.سورة العاديات
  • 101.سورة القارعة
  • 102.Aسورة التكاثر
  • 103.سورة العصر
  • 104.سورة الهمزة
  • 105.سورة الفيل
  • 106.سورة قريش
  • 107.سورة الماعون
  • 108.سورة الكوثر
  • 109.سورة الكافرون
  • 110.سورة النصر
  • 111.سورة المسد
  • 112.سورة الإخلاص
  • 113.سورة الفلق
  • 114.سورة الناس