1. ለሃሜተኛ ለዘላፊ ሁሉ ወዮለት፡፡
2. ለዚያ ገንዘብን የሰበሰበና የቆጣጠረው (ያደለበውም) ለኾነ ፤(ወዮለት)፡፡
3. ገንዘቡ የሚያዘወትረው መኾኑን ያስባል፡፡
4. ይከልከል፤ በሰባሪይቱ (እሳት) ውስጥ በእርግጥ ይጣላል፡፡
5. ሰባሪይቱም ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ?
6. የተነደደችው የአላህ እሳት ናት፡፡
7. ያቺ በልቦች ላይ የምትዘልቅ የኾነችው፡፡
8. እርሷ በእርግጥ በእነርሱ ላይ የተዘጋጀች ናት፡፡
9. በተዘረጋች አዕማድ ውስጥ (የተዘጋች ናት)፡፡